Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ አደም ፋራህ ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለ1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም በዓሉ የመልካም እሴቶች መገለጫ በሆኑት የመረዳዳት እና መተሳሰብ መንፈስ የተሞላ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

በጋራ የጀመርነውን የብልጽግና ጉዞ የምናጠናክርበትና ሀገራዊ አንድነታችንን ይበልጥ የምናጸናበት በዓል እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version