አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል መንግስት ከወሰነው የነዳጅ ታሪፍ በላይ እንዲሁም ከግብይት ሰንሰለት ውጪ ሲሸጡ በተገኙ ሁለት ማደያዎች ላይ ርምጃ ተወስዷል።
የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ርምጃ የተወሰደባቸው ማደያዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ተደጋጋሚ የጽሑፍና የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም ከሕገ ወጥ እንቅስቃሴያቸው ሊታቀቡ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
በዚህም ኤጀንሲው ማደያዎቹ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ምንም አይነት የነዳጅ ምርት እንዳይሸጡ የሚያስችል ርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡
በክልሉ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም መግለጻቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

