Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ማላቦ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ ኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ማላቡ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኡሳ ኡዙዌን ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
79 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈው የአፍሪካ፣ ካሪቢያንና ፓሲፊክ ሀገራት ድርጅት በአሁኑ ወቅት ከንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር በተጨማሪ የልማት፣ ዲፕሎማሲ፣ ፖለቲካዊ እና ዓለም አቀፍ የፍትህ ጉዳዮች የሚንሸራሸሩበት መድረክ እየሆነ መጥቷል።
11ኛው የአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና ፓስፊክ ሀገራት ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ከመጋቢት 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል።
በጉባኤው የአባል ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና የአውሮፓ ሕብረት ተወካዮች እንደሚገኙ ይጠበቃል።
Exit mobile version