አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ሱማሌ ተራ አካባቢ ያስገነባውን ባለ 27 ወለል ህንፃ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ህንፃውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አለምፀሐይ ጳውሎስ እና የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በጋራ መርቀውታል።
የ50 ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓሉን በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያከበረ የሚገኘው ተቋሙ÷ የመኖሪያ እና የንግድ ሆኖ የተገነባውን ህንፃ ነው ዛሬ በይፋ ያስመረቀው።

