Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ዞን አንድ የለማውን የሳርና መኖ ማምረቻ ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል ዞን አንድ አሳይታ ወረዳ የአዋሽ ወንዝን በመጠቀም የለማውን የሳር እና መኖ ማምረቻ ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ በ2 ሺህ 540 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው የሳርና መኖ ማምረቻ ፋብሪካው በአሳይታ ወረዳ በሚገኘው ኩዬት ላይቭስቶክ ፒ ኤል ሲ ኩባንያ የለማ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ከአንድ ሄክታር በአማካይ 36 ቶን መኖ እያመረተ የሚገኝ ሲሆን፥ ሳር ከማምረት ባለፈ የእንስሳት መኖ በፋብሪካ በማቀነባበር ለአካባቢው እና ለውጭ ገበያ እየቀረበ ይገኛል ተብሏል፡፡

በመስኖ ልማቱ ለእንስሳት የወተት ምርታማነት ወሳኝ የሆኑ የሳር አይነቶች እየተመረቱ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በመስኖ የሳር ልማት እና የመኖ ማቀነባበር ፋብሪካ ውስጥ 1ሺህ ሰራተኞች የሥራ እድል እንደተፈጠረላቸው ተገልጿል፡፡

ፋብሪካው ለአካባቢው ካለው የእንስሳት ሃብት ልማት አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ ከማበርከት በተጨማሪ ለሌማት ትሩፋት ሀገራዊ  ኢኒሼቲቭ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በለይኩን ዓለም

Exit mobile version