Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከነገ ጀምሮ የሚተገበር የኢንተርኔት እና የድምፅ ጥቅል ቅናሽ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ በኢንተርኔት ጥቅል እና በድምፅ ጥቅል አገልግሎቶቹ ላይ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ3 አመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ እና የ2013 በጀት አመትን ዋና የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በኢንተርኔት ጥቅል ላይ 35 በመቶ እንዲሁም በድምፅ ጥቅል ላይ የ29 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ገልፀዋል።

የሞባይል ድምጽ እና ዳታ ጥምር አገልግሎት 28 በመቶ እንዲሁም በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል አገልግሎት 21 በመቶ ቅናሽ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

በፕሪሚየም ያልተገደበ የዳታ ጥቅል አገልግሎት 21 በመቶ እንዲሁም በፕሪሚየም ያልተገደበ የድምጽ እና ዳታ ጥቅል አገልግሎት 20 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል፡፡

በፕሪሚየም ፕላስ ያልተገደበ የጥቅል አገልግሎት 16 በመቶ እንዲሁም በሳተላይት አገልግሎት ላይ እስከ 61 በመቶ ቅናሽ መደረጉም ተገልጿል፡፡

በቤትዎ ይቆዩ የጥቅል አገልግሎት ላይ የ59 በመቶ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን እስከ ፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ቀን ድረስ ባለበት እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያውያንን አዲስ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለአዲስ አመት የአደይ አበባ ጥቅል አገልግሎት 53 በመቶ እና በዓለም አቀፍ አየር ሰአት አገልግሎት ላይ የ100 ፐርሰንት የአየር ስጦታ ለደንበኞች አቅርቧል፡፡

በሶዶ ለማ

Exit mobile version