አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማ እና ውይይት መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

