አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ 70 እንደርታን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደርገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ሁዘይፋ ሻፊ እና ናትናኤል (2) ከመረብ አሳርፈዋል።
እንዲሁም ቀደም ብሎ ቀን 7 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የተደረገው የኢትዮጵያ ቡና እና ሸገር ከተማ ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።
በጨዋታው የኢትዮጵያ ቡናን ግብ አቡበከር አዳሙ ሲያስቆጥር÷ የሸገር ከተማን ደግሞ አሚር አብዶ ከመረብ አሳርፏል።
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ የተጀመረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 መሪነት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቅቋል።
እንዲሁም አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ምድረ ገነት ሽረ ከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታውን ያደርጋል።

