Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ ከቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይት አድርጌያለሁ ብለዋል።

በቆይታችን ወቅት በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ለማጠናከር ያለሙ በርካታ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ አከናውነናልም ነው ያሉት።

እነዚህ ውይይቶች እና የተፈረሙት ስምምነቶች ለሁለቱም ሀገራት የበለጸገ እና የተባበረ መጻኢ ዕድልን የሚያረጋግጡ፣ የቆዩ ግንኙነቶቻችንን ወደ ተጨባጭ ትብብር ለመቀየር እንደ ወሳኝ መሠረት የሚያገለግሉ የጋራ ቁርጠኝነታችን ማሳያ ጭምር ናቸው ሲሉም አብራርተዋል።

Exit mobile version