Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ አቀባበል አደረጉ

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ አቀባበል አድርገዋል።

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ የነገ ብሩህ ተስፋ እየተሰራባት ወደ ምትገኘው ምድረቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ብለዋል።

‎በቆይታዎ እጅግ ፍሬያማ ወይይት እንደሚኖረን እምነቴ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

Exit mobile version