Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደብረ ብርሃን እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

በደብረ ብርሃን ከተማ 10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የምግብ እና የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉን ያደረገው የኢትዮጵያ አዲስ ኪዳን መጥምቃዊት ቤተክርስቲያን ልማት ኮሚሽን ነው፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሔር  በዚህ ወቅት ÷ በከተማዋ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ለተደረገው ድገፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ 10 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ 11 አይነት የቤት ውስጥ እቃዎች፣ ምግብ እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው ብለዋል፡፡

መጋቢ ጵንኤል አጥላባቸው በበኩላቸው ዜጎች ቸግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚችሉትን ድጋፍ በማድረግ አብሮነታቸውን ማሳየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ወንጌል አማኞች ካውንስል ም/ሰብሳቢቄስ ደጉ ጌታቸው ÷ ቤተክርስያኗ እንደ ቃሉ የተራበን እያበላችና የታረዘን እያለበሰች ከሕዝብ ጎን በመቆሟ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል፡፡

 

http://በደብረ ብርሃን እርዳታ ለሚሹ ዜጎች የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

Exit mobile version