Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ስታዲየም የመሮጫ ትራክ አትሌቶች ልምምድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ስታዲየም ከ8 ዓመት በኋላ የመሮጫ ትራክ ተጠናቅቆ ዛሬ በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ ዓለም አቀፍ ውድድር ለሚሳተፉ አትሌቶች ክፍት በመደረግ ልምምድ ጀምረዋል።

ባለፉት ዓመታት በእድሳት ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ የነበረው ስታዲየሙ በአዲስ መልክ እድሳት ተደርጎለት ለውድድር እና ልምምድ ክፍት ተደርጓል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የፊታችን ቅዳሜ የሚደረገውን የአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ የአንድ ቀን ውድድር ስኬታማ እንዲሆን የመሮጫ መም እድሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ማድረጉን የኢትዮጵያ አቲሌትክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.