Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጂቡቲ የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጂቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አብዱልቃድር ሁሴን ኦማር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ዛሬ ጠዋት ከፕሬዚዳንት ኡመር ጌሌህ የተላከ መልዕክት በመያዝ የመጡትን የጂቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ተቀብዬ አነጋግሬያለሁ ብለዋል።

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው ትብብር መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version