አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል አለ።
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ኃይሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ከ46 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቋሚ የምርጫ ጣቢያዎች በዲጂታልና በማኑዋል አሰራር የመራጮች ምዝገባ ተከናውኗል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከዛሬ በደረሱ መረጃዎች ልዩ የምርጫ ጣቢያዎችን ሳይጨምር 50 ሚሊየን 514 ሺህ 155 ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል ነው ያሉት።
ከየካቲት 28/2018 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የመራጮች ምዝገባ በትናንትናው እለት መጠናቀቁ ይታወቃል።
በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫ ስራዎች እየተከወኑ መሆናቸውን ዋና ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።
በዙፋን ካሳሁን

