አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲት ጋር ቀጣናችንን መልክ በሚያሲዙ እና የጋራ መፃኢ የልማት ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
የሁለቱ ሀገሮች የላቀ እድገትና ተጠቃሚነት ዙሪያ መረጃ መለዋወጣቸውን ገልጸው÷ የኢኮኖሚ ትስስርን በጠንካራ ትብብር እና በኢንቨስትመንት በመደገፍ እድሎችን ማስፋት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር አድርገናል ነው ያሉት።