አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር ቼልሲ ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 11 ሰዓት ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኢንዞ ፈርናንዴዝ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ቼልሲ ለኤፍ ኤ ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ መድረሱን አረጋግጧል፡፡
በፍጻሜ ጨዋታም ቼልሲ ከማንቼስተር ሲቲ ጋር የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

