Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሞዛምቢክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ከፕሬዚዳንት ዳንኤል ፍራንሲስኮ ቻፖ ጋር በነበረን ቆይታ ዘላቂና ተጨባጭ ለውጥ ለሚያመጣ አጋርነት መሠረት የጣለ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

በተጨማሪም በስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩና የአሠራር ማዕቀፍ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የመግባቢያ ሰነዶችን ልውውጥ አካሂደናል ነው ያሉት።

Exit mobile version