አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተደራጅተው ስልጠና ለወሰዱ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታና ሼዶችን ሊያስተላልፍ ነው፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ በዛሬው ዕለት በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ 1ሺህ 278 ኢንተርፕራይዞችና 3ሺህ 889 አንቀሳቃሾች የመስሪያ ቦታ እና ሼዶች ይተላለፋሉ፡፡
የሚሰሩ እጆችን እናበረታታለን ያሉት ከንቲባዋ፥ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾቹ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው እንደየፍላጐታቸው ተደራጅው ስልጠና መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡

