አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሌ ክለል ሽንሌ ከተማ በፋራሕ ዋይስ ዱሌ አጠቃላይ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ተገኝተዋል፡፡
የኦክስጅን ፋብሪካው ለሲቲ ዞን ሁሉም ጤና ተቋማትና ለምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ኦክስጅን ማዳረስ እንደሚያስችል የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

