አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለቀጣናችን ሰላምና መረጋጋት መጠናከር መሰረት እንዲሆን እመኛለሁ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተመራጩ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ ታድመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ፕሬዚዳንቱ ለሀገራቸው የሚሰጡት አገልግሎት ሁለንተናዊ እድገትን እንዲያስቀጥል መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራት የቆየ ወዳጅነትና ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለሕዝቦቻችን የጋራ ብልጽግና እንዲሁም ለቀጣናችን ሰላምና መረጋጋት መጠናከር መሰረት እንዲሆን እመኛለሁ ነው ያሉት።

