Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማትና የኃይል ሽግግር የላቀ ሚናዋን ትቀጥላለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማትና የኃይል ሽግግር የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን ትቀጥላለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ፎርዋርድ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና በፈረንሳይ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን በጋራ ባዘጋጁት ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አካፍያለሁ ብለዋል።

በተለይም የአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት እና የኃይል ሽግግርን በተመለከተው የውይይት መድረክ ላይ ከተሞክሯችን የተቀዱ ከፍ ያሉ ሀሳቦች ተነስተዋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በሁለቱ ዘርፎች የጀመረችውን ስራ በማጠናከር የላቀ ሚና መጫወቷን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

Exit mobile version