Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ አቶ ዘገየ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች የዘመናት ፍትሃዊ ጥያቄ የሆነው መሬት ለአራሹ መልስ እንዲያገኝ በግንባር ቀደምትነት ጉልህ አስተዋፆኦ ያደረጉ ተራማጅ ሰው እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

ትውልዱ ምንጊዜም ያስታውሳቸዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ አቶ ዘገየ አስፋው በማረፋቸው ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version