አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ ልማትና የመረጃ ሉዓላዊነት ላይ ያተኮረ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡
“የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት” በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያስመገበቻቸው ስኬቶችና የወደፊት አቅጣጫዎች በጥልቀት ይዳሰሳሉ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፥ ኢትዮጵያ የልማት ትልሞቿን እንዲሁም ስኬቶቿን በመረጃና በአሃዛዊ ማስረጃ መሰነድ ከጀመረች ሰነባብታለች።
ይህ ርምጃ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሌሎች በሚደገፉና በተበታተኑ የመረጃ ቋቶች ላይ የነበራትን ሙሉ ጥገኝነት ለመቅረፍ ያሳየችውን ከፍተኛ ቁርጠኝነት ማረጋገጫ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ይህ አዲስ ምዕራፍ የሀገሪቱን የመረጃ ሉዓላዊነት በተግባር በማረጋገጥ ኢትዮጵያ በራሷ መረጃ ላይ ተመስርታ እንድትወስንና የራሷን የልማት መስመር እንድትተልም ያስቻለ መሆኑንም ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

