Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከሩዋንዳ ከመጡ 128 የሕክምና ባለሙያዎች ጋር ማዕድ ቆርሰናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በልዩ የሕክምና ዘርፍ ሥልጠና ላይ ከሚገኙ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከመጡ ከ400 በላይ የሕክምና ባለሙያዎች መካከል ከሩዋንዳ ከመጡ 128 የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በጋራ ማዕድ ቆርሰናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ባለሙያዎቹ የአሕጉራችን የጤና ዘርፍ የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚጠይቀውን ከፍተኛ ዕውቀትና የላቀ ብቃት ለማሟላት ታምነው እየተጉ ያሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ቀጣዩን አፍሪካዊ ትውልድ በሕክምና ዘርፍ የሚኖረውን የመሪነት ሚና በማረጋገጥ ላይ የሚገኙ ተቋማት አካል ናቸውም ብለዋል።

‎በጋራ ዕውቀትና ዓላማ ይበልጥ ጤናማ የሆነች አፍሪካን አብረን መገንባታችንን እንቀጥላለን ሲሉም አመልክተዋል።

Exit mobile version