Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብልፅግና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገሩ ባሕር ዳር ሕያው ምስክር ናት – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገሩ ባሕር ዳር ሕያው ምስክር ናት አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በባሕር ዳር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ብልፅግና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር እያሸጋገራት መሆኑን ተናግረዋል።
ባሕር ዳር ብልፅግና ሰው ሆኖ የሚንቀሳቀስባት ሕያው ማሳያ ናት ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የባሕር ዳር ሕዝብ ስለ ብልጽግና አስረጂ አያሻውም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
አዲሱ የዓባይ ድልድይ፣ የኮሪደር ልማት፣ የዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናልና የኢኮ ሪዞርቶች ግንባታና የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት በብልፅግና ዘመን በንግግር ሳይሆን በተግባር የተመዘገቡ የባሕር ዳርና የክልላችን እውነታዎች ናቸው ብለዋል፡፡
ብልፅግና ስለ አማራ ሕዝብ ለዘመናት የነበረውን የተሳሳተ ትርክት ያረመና ዕሴቶቹን ከፍ ያደረገ ፓርቲ መሆኑን በማውሳት፥ ለክልሉ ሕዝብ ከብልፅግና የተሻለ ዘመን አይመጣም ነው ያሉት፡፡
ፈተናዎቻችን ብዙ ቢሆኑም አቅማችንና ቆራጥነታችን ከፈተናዎቻችን በላይ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢትዮጵያን ትንሳኤና መበልጸግ እውን ለማድረግ ዜጎች ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጡ ጠይቀዋል።
Exit mobile version