Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቦረና ዞን የመስኖ ግድቦች ግንባታ መጠናቀቅ የውሃ መሠረተ ልማትን የማረጋገጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቦረና ዞን የመስኖ ግድቦች ግንባታ መጠናቀቅ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም የውሃ መሠረተ ልማትን የማረጋገጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የሚያሳይ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በፊና ኦሮሚያ የመስኖ ፕሮጀክቶች አማካኝነት በጎሞሌ ወረዳ ቦረና ዞን የመስኖ ግድቦች ግንባታ መጠናቀቅ የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም የውሃ መሠረተ ልማትን የማረጋገጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

ይኸው እጅግ አስፈላጊ የሆነ መሠረተ ልማት በደሴ ጎራ ከ190 ሚሊየን ኩቢክ ሜትር በላይ የሚሆን ከፍተኛ የውሃ ክምችት መያዝ የሚችል አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው የውሃ አቅርቦት እንዲኖር ያደርጋልም ነው ያሉት።

በተጨማሪም ፕሮጀክቶቹ ከ14 ሺህ 500 ሄክታር በላይ የሚሆን የግብርና መሬትን በመስኖ የማልማት አቅም ያለው በመሆኑ እያንዳንዱን ቤተሰብ በቀጥታ ለመደገፍ፣ የምግብ ምርትን ለማጠናከር እና ለከብቶች የሚሆን የውሃ ሀብትን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያስችላሉ ብለዋል።

Exit mobile version