Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቦረና ባሕል ማዕከልን አስመረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በያቤሎ ከተማ የሚገኘውን የቦረና ባሕል ማዕከል በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

በ57 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ መሆኑን ገልጸው÷ በአንድ ጊዜ እስከ 2 ሺህ ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና የቅርስ ሙዚየምን አካቶ የተገነባ ነው ብለዋል።

ማዕከሉ የቦረናን ሕዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና ፍልስፍና ለትውልድ የማሸጋገር ቁልፍ ሚና ይኖረዋልም ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

Exit mobile version