Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግሥታት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎችን እየጎበኙ ነው፡፡
የታዛቢ ቡድኑ መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎችን አከፋፈት እና አጠቃላይ የምርጫውን ሒደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
መሪዋ የመጀመሪያ ምልከታቸውን ያደረጉት በምርጫ ክልል 17፣ ወረዳ 3 በሚገኘው የሻላ ፓርክ ምርጫ ጣቢያ ቁጥር 1 ላይ ሲሆን÷ በዚህም የምርጫ ቁሳቁሶች መሟላታቸውን፣ የጣቢያውን አከፋፈት ሕጋዊ ሥነ ሥርዓት እና የድምፅ አሰጣጥ ጅማሮን በቅርበት ታዝበዋል።
የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን እየተካሄደ የሚገኘውን የድምፅ አሰጣጥ ሒደት፣ የመራጮችን ተሳትፎ፣ የምርጫ ጣቢያዎችን ለአካል ጉዳተኞችና ለአረጋውያን ምቹ መሆን እንዲሁም አጠቃላይ የጸጥታና የምርጫ ድባቡን በቅርበት መከታተሉን እንደሚቀጥል የኢጋድ መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version