አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ክልሎች የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
በትናንትናው ዕለት በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ ቆጠራ ተጠናቅቆ ጊዜያዊ ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ እየተለጠፈ ይገኛል፡፡
በተጨማሪም በምርጫ ጣቢያዎች የሚገኙ የምርጫ ቁሳቁሶች ወደ ምርጫ ክልሎች እየተሰበሰቡ መሆኑን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

