አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉሪቱ ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ አሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ መሪ የሆኑትን የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የስራ ባልደረቦቻቸውን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል።
73 አባላትን የያዘው የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከተው አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን ነው ያሉት።
ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉሪቱ ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ አንስተዋል።
የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅናና አድናቆት እየሰጠን የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን ብለዋል።

