Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከኖርዌይ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፤ በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ – አፍሪካ ኢቪ ላይ በጋራ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል።
አዲስ አበባ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተችና ተመራጭ እየሆነች መምጣቷን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አመልክተዋል።
የኖርዲክ – አፍሪካ ኢቪ ጉባኤንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እናሳካዋለን ብለዋል።
Exit mobile version