አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ1 ሺህ 139 የምርጫ ክልል ውጤቶች 1 ሺህ 131 ያህሉ ወደ ማረጋገጫ ማዕከል ደርሰዋል አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ።
ሰብሳቢዋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ አሁን ላይ ከ501 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ምርጫ ክልሎች ውስጥ 497ቱ ወደ ማረጋገጫ ማዕከል ደርሰዋል፡፡
እንዲሁም ከ638 የክልል ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች 634ቱ ወደ ቦርዱ ማረጋገጫ ማዕከል መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
120 የሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ቅሬታ መቅረቡን ጠቅሰው÷ ጉዳዩ በሕግ ባለሙያዎች እየተጣራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
148 ምስክሮች በተለያዩ ቅሬታዎች ላይ ምስክርነታቸውን መስጠታቸውንም ነው የገለጹት፡፡
በሶስና አለማየሁ

