አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከስምንት ቢሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ሆነዋል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት ጽሑፍ ÷ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ለዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከስምንት ቢሊየን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት አረንጓዴ ለሆነች ነገ፣ ሁላችንም ተስፋን እንትከል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

