አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ የዚህን ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምረናል።
በተያዘው ዓመት 8 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ግብ መቀመጡን ገልጸው ÷ በዚህም 65 ቢሊየን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በጽናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ዜጎች ንቅናቄውን ተቀላቅለው ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ዐሻራቸውን እንዲያኖሩም ጥሪ አቅርበዋል።

