Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የምህንድስና እና የጤና ዘርፎች ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የምህንድስና እና የጤና ዘርፎች በመደበኛ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 502 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርስቲው በተለያዩ የምህንድስና እና የጤና ዘርፎች በመደበኛ ፕሮግራም በሁለተኛ ዲግሪ በባችለር ዲግሪ እና በቲቬቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው ያስመረቀው።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌድሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ ተገኝተዋል ።

በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ እንደተናገሩት ሠራዊቱ ለውጡን የሚሸከም በርካታ የሪፎርም ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።

ሠራዊቱ ከፖለቲካ፣ ከብሄርና ከሀይማኖት ወገንተኝነት ነፃ የሆነና ፕሮፌሽናል ሆኖ እንደሚገነባ ያስታወቁት ጀነራል አደም ግዳጁን ለመወጣት የሚያስችሉ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መዘመን እንዳለባቸውና ለዚህም ተቋሙ እስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል ።

ዩንቨርሲቲው ላለፉት 19 ዓመታት በተለያዪ የኢንጂነሪንግ፣ የጤና እና የሀብት አስተዳደር ዘርፎች ተማሪዎችን አስተምሮ ሲያስመርቅ መቆየቱ የተገለፀ ሲሆን፥ በዛሬው እለት የተመረቁትን ጨምሮ በአጠቃላይ እስካሁን 9 ሺህ 856 ተማሪዎችን ማስመረቁን አስታውቋል።

በትዝታ ደሳለኝ

Exit mobile version