አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን ትኩረት እየሳበ ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልሰ አብዲሳ፡፡
አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የገዳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የኦሮሞ ሕዝብን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቋቋመ ነው፡፡
በኢኮኖሚ ዞኑ በአሁኑ ወቅት ባለሃብቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የኢንቨስትመንት ሥራ መጀመራቸውን አመልክተዋል፡፡
በዚህ መሰረትም ባለሃብቶች በንግድ፣ ሎጂስቲክስ፣ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን እና በሌሎች ዘርፎች ሥራ ጀምረዋል ነው ያሉት፡፡
በኢኮኖሚ ዞኑ ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶችን ጨምሮ የአሜሪካ፣ ቻይና፣ የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች፣ ኔዘርላንድስ፣ ጣሊያን እና የሌሎች ሀገራት ባለሃብቶች መሰማራታቸው ተጠቅሷል፡፡

