Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 438 መቀመጫ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብልጽግና ፓርቲ 438 መቀመጫዎችን አሸንፏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤትን ይፋ አድርገዋል።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ከፍተኛ መቀመጫ ያገኘ ፓርቲ መንግሥት መመስረት እንደሚችል ይታወቃል።

ጠቅላላ ምርጫው በ1ሺህ 139 ምርጫ ክልሎች ላይ የተካሄደ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የ501 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በክልል ምክር ቤት ከ638 የምርጫ ክልሎች ላይ መካሄዱ ይታወቃል።

Exit mobile version