የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የተከበሩ ወንድሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልጽግና ፓርቲ በምርጫው በማሸነፋቸው በአፍሪካ ህብረት እና በቡሩንዲ ስም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
ይህ የታደሰ ዴሞክራሲያዊ ኃላፊነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ብሎም ኢኮኖሚያዊ እድገት በእርስዎ አመራር ላይ ያለውን መተማመን ያንጸባርቃል በማለት አክለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ የእርሷ ጥንካሬ፣ አንድነትና ብልጽግና ለአፍሪካዊያን የጋራ አጀንዳ ስኬት መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም በትብብር በመስራትና በጋራ በመቆም ቀጣናዊ ግንኙነትን በማጠናከር ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች የሚለውን እሳቤ ማጽናት እንደሚገባ ገልጸው፤ በጋራ የበለጸገች፣ ሰላማዊና አንድነቷ የጸና አፍሪካን መገንባታችንን እንቀጥላልን ብለዋል በመልዕክታቸው።

