አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ የማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለአየር ንብረት ጥበቃ መሠረታዊ አስተዋፅዖ እያበረከተ ነው ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የማር ምርት ላይ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ተፈጥሮንና አካባቢያችንን በመጠበቃችን፣ ደኖች እየተስፋፉ በመምጣታቸው፣ የንብ ዝርያዎችን የሚያግዙና የማር ምርትን የሚያሳድጉ ምቹ ከባቢዎች ምክንያት የምግብ ምንጮች ሊፈጠሩ ችለዋል ሲሉም አውስተዋል፡፡

