Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፈረንሳይ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፈረንሳይ መንግሥት በኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የፈረንሳይ መንግሥት በመልዕክቱ÷ አዲስ የተመረጡ የፓርላማ አባላትን፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን እንዲሁም በሒደቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና የሲቪክ ማኅበራትን አድንቋል፡፡

በምርጫው በንቃት በመሳተፍ ስኬታማ በሆነ መንገድ ላከናወነው የኢትዮጵያ ሕዝብም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ማስተላለፉን በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version