አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሃሙድ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሃሙድ ጋር በኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ ደኅንነትና የቀጣናዊ መረጋጋት ዙሪያ በመተማመንና በመከባበር ላይ የተመሠረተ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።
ኢትዮጵያና ሶማሊያ ከድንበር በላይ የሚጋሩት ነገር አለ ፤ እሱም እጅግ ውድ የሆነውን ሕዝባችንን እና የጋራ እጣ ፈንታችንን ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

