Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቱሪዝም ሀብታችንን በልኩ ለመጠቀም የመሰረተ ልማት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ባላት ከፍተኛ የቱሪዝም ሀብት በተገቢው ልክ ለመጠቀም የቱሪዝም መሰረተ ልማት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር” በሚል በቱሪዝም ዙሪያ ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፥ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ፀጋዎችና የቱሪዝም አቅም ለዓለም ማስተዋወቅ ይገባል፡፡

ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የዕፅዋት ዝርያዎች፣ ታሪካዊ ስፍራዎች፣ ብርቅዬ የዱር እንስሳትና ድንቅ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር መገኛ መሆኗን አመልክተዋል፡፡

ከራስ ዳሸን እስከ ዳሎል ከፍተኛና ዝቅተኛ ቦታዎች የሚገኙባት እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት በተለየ መልኩ የተለያዩ የአየር ፀባዮችን የምታስተናገድ ሀገር መሆኗንም አውስተዋል፡፡

ሆኖም የኢትዮጵያ የቱሪዝም አቅም በተገቢው ልክ አለመልማቱን ገልጸው፥ መዳረሻዎችን አለመለየትና መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ መገንባት አለመቻል በዘርፉ እድገት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያን ዕምቅ አቅም በተገቢው መልኩ ለማልማት የኢትዮጵያን ፀጋዎች መገንዘብ፣ መሰረተ ልማት ማስፋፋትና የቱሪዝም ጸጋዎችን የማስተዋወቅ ስራ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ይህን ማደረግ ከተቻለ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የቱሪስት መዳረሻዎች አንዷ መሆን ትችላለች ነው ያሉት፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version