Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

እንግሊዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎን በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛው ዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ እንግሊዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎን 2 ለ 1 በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅላለች።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በአትላንታ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የእንግሊዝን የማሸነፊያ ግቦች ሃሪ ኬን አስቆጥሯል፡፡
ዲሞክራቲክ ኮንጎ በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ እንዲሁም አስቀድማ ግብ በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ ብትችልም አሳዛኝ ተሸናፊ በመሆን ከውድድሩ ተሰናብታለች፡፡
እንግሊዝ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ከሜክሲኮ ጋር በ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ትፋለማለች፡፡
Exit mobile version