አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት በጠንካራ ስራ በሀገር ውስጥ በማልማት የኢኮኖሚ ልዕልናችንን የምናረጋግጥበት ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የሀገር ውስጥ ምርትን በራስ አቅም ማሳደግ የኢኮኖሚ ነጻነታችንና የሉዓላዊነታችን መሰረት ነው ብለዋል።
በዛሬው ዕለት በጋሞ ዞን በወርሃ ነሐሴ 2017 ዓ.ም ሥራ የጀመረው ‘ዮ ሆልዲንግ’ የድንጋይ ከሰል ፋብሪካን የስራ ሂደት ጎብኝተናል ብለዋል።
ፋብሪካው የኢንዱስትሪዎቻችንን ፍላጎት በሀገር ውስጥ በመተካት ከውጭ የሚገባ ምርትን አስቀርቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ለአካባቢው ነዋሪዎችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን አመልክተዋል።

