አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የኮፕ32 ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከኮፕ 30 ፕሬዚዳንት አምባሳደር አንድሬ አራንሃ ኮሪያ ዶ ላጎ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 32) አስተናጋጅ ለመሆን በምታደርገው ዝግጅት ላይ፣ ከቀደምት አዘጋጅ ሀገራት ልምድ መቅሰም ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ ተነስቷል።
ከኮፕ 30 ፕሬዚዳንት አምባሳደር አንድሬ አራንሃ ኮሪያ ዶ ላጎ እና ከቡድናቸው ጋር የተደረገው የሁለትዮሽ ውይይትም ይሄንኑ ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
ውይይቱ ዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ጉባዔ ከማዘጋጀት ጋር የተያያዙ ዕውቀቶችን እና የተወሰዱ ትምህርቶችን መለዋወጥ ላይ ያተኮረ መሆኑን የኮፕ32 ኢትዮጵያ መረጃ ያመላክታል፡፡

