ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- abel neway 2 hours ago ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ያካሄደችው የኢኮኖሚ ሪፎርሙ እንደ ሀገር ጸንታ እንድትቀጥል አስችሏል፡፡ በሪፎርሙ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከነበረበት ችግር እና አረንቋ በመጠኑም ቢሆን ወጥቷል፡፡ በግብርና ዘርፍ በክላስተር፣ በማሽን ማስፋት፣ መሬት ማስፋት እና በመስኖ ስራዎች ላይ የተሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል፤ ዘንድሮ 29 ሚሊየን ሄክታር መሬት ታርሶ ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል፡፡ በሌማት ትሩፋት የተጀመረው ስራ አስደናቂ ውጤት እያስገኘ ነው፤ በፍራፍሬ በተለይም በአቮካዶ በአፍሪካ ሁለተኛዋ ላኪ ሀገር በመሆን ከፍተኛ ገቢ አግኝተናል፡፡ ለብዙ ጊዜ በድርቅ እና ረሃብ የሚታወቀው ቦረና ከፍተኛ የስንዴ ምርት አስገኝቷል፤ በሶማሌ እና አፋር ክልሎችም ሰፋፊ የእርሻ ማሳዎች የሚታዩበት ሲሆን፤ እርሻ ላይ አበክረን ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደምንችል ያየንበት ነው፡፡ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ከለውጡ በፊት የነበሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው ከ47 በመቶ በታች ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የኃይል፣ የመሬት እና የፋይናንስ ችግር የነበረባቸው ሲሆን፤ ኮሚቴ ተቋቁሞ ችሮቻቸውን መፍታት በመቻላችን ቀድሞ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች አሁን ላይ 67 በመቶ ማምረት ችለዋል፡፡ ከኮምቦልቻ፣ መቐለ እና ሀዋሳ ውጪ ከ10 ያላነሱ ኢንዱስሪ ፓርኮች የገነባነው እኛ ነን፣ የግሉን ዘርፍ እና የውጭ ባለሀባቶችን ያስገባነው እኛ ነን፡፡ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የመጣው በጣም ወሳኝ እድገት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከውጭ ታስገባ የነበሩ የሴራሚክ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት እና መስታወት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት ችላለች፡፡ በተጨማሪም የማዕድን፣ ኃይል እና ማኑፋክቸሪንግ ላይ ሰፋፊ እድገት መጥቷል፡፡ በአቤል ነዋይ