Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ያካሄደችው የኢኮኖሚ ሪፎርሙ እንደ ሀገር ጸንታ እንድትቀጥል አስችሏል፡፡
👉 በሪፎርሙ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከነበረበት ችግር እና አረንቋ በመጠኑም ቢሆን ወጥቷል፡፡
👉 በግብርና ዘርፍ በክላስተር፣ በማሽን ማስፋት፣ መሬት ማስፋት እና በመስኖ ስራዎች ላይ የተሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል፤ ዘንድሮ 29 ሚሊየን ሄክታር መሬት ታርሶ ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል፡፡
👉 በሌማት ትሩፋት የተጀመረው ስራ አስደናቂ ውጤት እያስገኘ ነው፤ በፍራፍሬ በተለይም በአቮካዶ በአፍሪካ ሁለተኛዋ ላኪ ሀገር በመሆን ከፍተኛ ገቢ አግኝተናል፡፡
👉 ለብዙ ጊዜ በድርቅ እና ረሃብ የሚታወቀው ቦረና ከፍተኛ የስንዴ ምርት አስገኝቷል፤ በሶማሌ እና አፋር ክልሎችም ሰፋፊ የእርሻ ማሳዎች የሚታዩበት ሲሆን፤ እርሻ ላይ አበክረን ከሰራን ውጤት ማምጣት እንደምንችል ያየንበት ነው፡፡
👉 በኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ከለውጡ በፊት የነበሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው ከ47 በመቶ በታች ነበር፡፡
👉 አንዳንዶቹ የኃይል፣ የመሬት እና የፋይናንስ ችግር የነበረባቸው ሲሆን፤ ኮሚቴ ተቋቁሞ ችሮቻቸውን መፍታት በመቻላችን ቀድሞ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች አሁን ላይ 67 በመቶ ማምረት ችለዋል፡፡
👉 ከኮምቦልቻ፣ መቐለ እና ሀዋሳ ውጪ ከ10 ያላነሱ ኢንዱስሪ ፓርኮች የገነባነው እኛ ነን፣ የግሉን ዘርፍ እና የውጭ ባለሀባቶችን ያስገባነው እኛ ነን፡፡ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የመጣው በጣም ወሳኝ እድገት ነው፡፡
👉 ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከውጭ ታስገባ የነበሩ የሴራሚክ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት እና መስታወት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት ችላለች፡፡
👉 በተጨማሪም የማዕድን፣ ኃይል እና ማኑፋክቸሪንግ ላይ ሰፋፊ እድገት መጥቷል፡፡
በአቤል ነዋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.