Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የ2019 በጀት 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል መንግስት የ2019 በጀት 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2019 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርቧል፡፡

በዚህም መሰረት 2 ነጥብ 34 ትሪሊየን ብር ሆኖ የቀረበውን የፌደራል መንግስት የ2019 በጀት ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የፀደቀው ጠቅላላ በጀት ከ2018 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ411 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወይም 21 ነጥብ 3 በመቶ እድገት እንዳለው ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version