አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለሶስት አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
ፕራይዝዎርዝ ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ ፈቃድ ከተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
በተጨማሪም ብሉፊን ካፒታል አድቫይዘሪ ኃ.የተ.የግ.ማ እና ሉሚና ካፒታል ኃ.የተ.የግ.ማ በሰነደ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት ማማከር ዘርፍ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም በባለስልጣኑ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ጠቅላላ ቁጥር 21 ደርሷል፡፡
ባለስልጣኑ አገልግሎት ሰጪዎቹ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሁሉን ባለሃብቶች ባማከለ መልኩ በዕውቀት፣ በታማኝነት እንዲሁም በቁርጠኝነት እንዲሰሩ አሳስቧል፡፡
በሌላ በኩል የሶስቱ አዳዲስ አገልግሎት ሰጪዎች 10 ተሿሚ እንደራሴዎች እንዲሁም የ15 ቦርድ አባላት ሹመት ፈቃድ መጽደቁን የባለስልጣኑ መረጃ አመልክቷል፡፡
ለሶስት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ ተሰጠ

