አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀድሞው የኳታር አሚር ሼይኽ ሀማድ ቢን ካሊፋ አልታኒ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት፥ ለልዑል አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል-ታኒ እንዲሁም ለኳታር ሕዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ሼይኽ ሀማድ ለኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት መስጠታቸውንና በሁለቱ ሀገራት መካከል ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለመፍጠር ጽኑ አቋም እንደነበራቸው አስታውሰው፥ በዚህም በኢትዮጵያውያን ዘንድ በከፍተኛ ክብር ይታወሳሉ ነው ያሉት፡፡
በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን፣ ለውይይትና ለድርድር መሰረት ለመጣል እንዲሁም ግጭቶችን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ኳታር እና አፍሪካ እኚህን አስተዋይ መሪ አጥተዋል ብለዋል።

